watermark logo

Up next

Autoplay

እያንገላታኝ ነው; ሳሚ-ዳን (EYANGELATAGN NEW) Sami-Dan; Official New Ethiopian Music Video

0 Views • 08/02/24
Share
Embed
videosep
videosep
504 Subscribers
504

🌕 እያንገላታኝ ነው 🌕

መሬት የማይነካኝ ባየር ላይ ነጣሪ
ሽቅርቅር አማላይ ነገር አሳማሪ
ከኔ በላይ ማነው ብዬ ምፎክር
ነበርኩ እኔ ላገር ማስቸግር

ወይ ጊዜ ወይ እጣ ክፉ ቢገጥመኝ
ፍቅር ጠልፎ ጥሎ ከቤት አዋለኝ
ትቢቴን አንጥፎ ከመሬት የጣለው
ፍቅርሽማ እያንገላታኝ ነው

ጠዋት እስከ ማታ - እያንገላታኝ ነው
ሆነሽ ሁሉም ቦታ - እያንገላታኝ ነው
እኔስ ምን ላድርግሽ ውዴ የኔ ገላ
ፍቅርሽማ - እያንገላታኝ ነው

የኔ እንዲያ መገንፈል ሀገር ማጥለቅለቁ
አውቀው አሳለፉኝ ቀን እየጠበቁ
በጉልበት ላይ ጉልበት ሲመጣ ድንገት
ያስጨንቃል ያስብላል ወዴት

በሰከነ መንፈስ በረጋው ቃልሽ
ስታነጋግሪኝ ኩራቴን ጥሰሽ
ስንት እርቀት ሄደሽ ነካካሽኝ ይኸው
ፍቅርሽማ እያንገላታኝ ነው

ጠዋት እስከ ማታ - እያንገላታኝ ነው
ሆነሽ ሁሉም ቦታ - እያንገላታኝ ነውi
እኔስ ምን ላድርግሽ ውዴ የኔ ገላ
ፍቅርሽማ - እያንገላታኝ ነው

አቅሜን ያጣሁ ሰው ነኝ - አቅሜን አጣሁኝ ዛሬ
አንገቴን እያስደፋኝ - ባንቺ ሰው መቸገሬ
አንቺ እንደኔ አይደለሽ - እንደኔማ አይደለሽ
ድረሽልኝ በሞቴ - ነይ ባክሽ ቶሎ ብለሽ

መዳን ነው ይሉኛል- መዳን ነው ይሉኛል ሁሉም
ፍቅር የነካው ሰው - ፍቅር ነው ሚወጣው ቃሉ
አንቺን ምክንያት አርጎ - ፍቅርማ እኔን ካዳነ
ሁሉንም ልቀበል - ልቤም ይሁን የታመነ

ጠዋት እስከ ማታ - እያንገላታኝ ነው
ሆነሽ ሁሉም ቦታ - እያንገላታኝ ነው
እኔስ ምን ላድርግሽ ውዴ የኔ ገላ
ፍቅርሽማ - እያንገላታኝ ነው

Show more
0 Comments sort Sort By

Up next

Autoplay